9 “ሁለት የኦኒክስ ድንጋዮችን+ ወስደህ የእስራኤልን ወንዶች ልጆች ስሞች+ ትቀርጽባቸዋለህ፤ 10 በትውልዳቸው ቅደም ተከተል መሠረት የስድስቱን ስሞች በአንዱ ድንጋይ ላይ፣ የቀሩትን የስድስቱን ስሞች ደግሞ በሌላኛው ድንጋይ ላይ ትቀርጻለህ። 11 አንድ ቅርጽ አውጪ በድንጋይ ላይ ማኅተም እንደሚቀርጽ ሁሉ የእስራኤልን ወንዶች ልጆች ስሞች በሁለቱ ድንጋዮች ላይ ይቀርጽባቸዋል።+ ከዚያም በወርቅ አቃፊዎች ውስጥ እንዲቀመጡ ታደርጋለህ።