-
ዘፀአት 25:2-7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 “ለእስራኤላውያን መዋጮ እንዲያመጡልኝ ንገራቸው፤ ለመስጠት ልቡ ካነሳሳው ከእያንዳንዱ ሰው መዋጮዬን ትቀበላላችሁ።+ 3 ከእነሱ የምትቀበሉት መዋጮም ይህ ነው፦ ወርቅ፣+ ብር፣+ መዳብ፣+ 4 ሰማያዊ ክር፣ ሐምራዊ ሱፍ፣* ደማቅ ቀይ ማግ፣ ጥሩ በፍታ፣ የፍየል ፀጉር፣ 5 ቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፣ የአቆስጣ ቆዳ፣ የግራር እንጨት፣+ 6 ለመብራት የሚሆን ዘይት፣+ ለቅብዓት ዘይትና+ ጥሩ መዓዛ ላለው ዕጣን+ የሚሆን በለሳን፣ 7 ለኤፉዱ+ እንዲሁም ለደረት ኪሱ+ የሚሆኑ የኦኒክስ ድንጋዮችና ሌሎች ድንጋዮች።
-
-
ዘፀአት 35:29አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
29 ልባቸው ያነሳሳቸው ወንዶችና ሴቶች በሙሉ ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት እንዲከናወን ላዘዘው ሥራ የሚውሉ ነገሮችን አመጡ፤ እስራኤላውያኑ ይህን በፈቃደኝነት የሚቀርብ መባ አድርገው ለይሖዋ አመጡ።+
-