-
ዘሌዋውያን 12:6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 ሴትየዋ ወንድ ልጅ ወይም ሴት ልጅ ወልዳ የመንጻቷ ጊዜ ሲያበቃ ለሚቃጠል መባ እንዲሆን አንድ ዓመት ገደማ የሆነው የበግ ጠቦት፣+ ለኃጢአት መባ እንዲሆን ደግሞ አንድ የርግብ ጫጩት ወይም አንድ ዋኖስ ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ወደ ካህኑ ታመጣለች።
-
-
ዘሌዋውያን 22:18-20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 “ለአሮን፣ ለወንዶች ልጆቹና ለእስራኤላውያን በሙሉ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ስእለቱን ለመፈጸም ወይም የፈቃደኝነት መባ ለማቅረብ+ ሲል የሚቃጠል መባውን ለይሖዋ የሚያቀርብ አንድ እስራኤላዊ ወይም በእስራኤል ውስጥ የሚኖር አንድ የባዕድ አገር ሰው+ 19 ተቀባይነት እንዲያገኝ ከፈለገ መሥዋዕቱ ከመንጋው፣ ከጠቦቶቹ ወይም ከፍየሎቹ መካከል የተወሰደ እንከን የሌለበት ተባዕት+ መሆን ይኖርበታል። 20 ተቀባይነት ስለማያስገኝላችሁ እንከን ያለበትን ማንኛውንም ነገር አታቅርቡ።+
-