ዘፀአት 27:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 አመዱን* ማስወገጃ ባልዲዎችን፣ አካፋዎችን፣ ሳህኖችን፣ ሹካዎችንና መኮስተሪያዎችን ትሠራለህ፤ ዕቃዎቹንም ሁሉ ከመዳብ ትሠራቸዋለህ።+ ዘሌዋውያን 1:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ቋቱንና ላባዎቹንም ከለየ በኋላ ከመሠዊያው አጠገብ በስተ ምሥራቅ በኩል ወዳለው አመድ* ወደሚደፋበት ቦታ ይወርውራቸው።+