የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፀአት 29:16-18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 አንተም አውራውን በግ እረደው፤ ደሙንም ወስደህ በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ እርጨው።+ 17 አውራውንም በግ በየብልቱ ቆራርጠው፤ ሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም እጠባቸው፤+ ከዚያም የተቆራረጡትን ብልቶች ከጭንቅላቱ ጋር አሰናድተህ አስቀምጣቸው። 18 አውራውንም በግ ሙሉ በሙሉ በማቃጠል በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ አድርገው። ይህም ለይሖዋ የሚቀርብ የሚቃጠል መባ ይኸውም ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ+ ነው። ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ነው።

  • ዘሌዋውያን 8:18-21
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 18 እሱም ለሚቃጠል መባ የሚሆነውን አውራ በግ አመጣ፤ አሮንና ወንዶች ልጆቹም እጆቻቸውን በአውራው በግ ራስ ላይ ጫኑ።+ 19 ከዚያም ሙሴ አውራውን በግ አረደው፤ ደሙንም በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ረጨው። 20 አውራውንም በግ በየብልቱ ቆራረጠው፤ ቀጥሎም ጭንቅላቱን፣ ብልቶቹንና ሞራውን* አጨሰው። 21 ሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም በውኃ አጠባቸው፤ ሙሴም አውራው በግ በሙሉ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ አደረገ። ይህም ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው የሚቃጠል መባ ነበር። ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ነበር።

  • ዘሌዋውያን 9:12-14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 ከዚያም የሚቃጠል መባ ሆኖ የሚቀርበውን እንስሳ አረደው፤ ወንዶች ልጆቹም ደሙን ሰጡት፤ እሱም ደሙን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ረጨው።+ 13 እነሱም የሚቃጠለውን መባ ብልቶች ከነጭንቅላቱ ሰጡት፤ እሱም በመሠዊያው ላይ እንዲጨሱ አደረገ። 14 በተጨማሪም ሆድ ዕቃውንና እግሮቹን አጠባቸው፤ በመሠዊያው ላይ ባለው በሚቃጠለው መባ ላይም እንዲጨሱ አደረገ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ