ዘሌዋውያን 6:25, 26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 “አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እንዲህ በላቸው፦ ‘የኃጢአት መባ ሕግ ይህ ነው፦+ ለኃጢአት መባ የሚሆነውም እንስሳ፣ ለሚቃጠል መባ የሚሆነው እንስሳ በሚታረድበት ቦታ+ በይሖዋ ፊት ይታረዳል። ይህ እጅግ ቅዱስ የሆነ ነገር ነው። 26 ይህን ለኃጢአት መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርበው ካህን ይበላዋል።+ በመገናኛ ድንኳኑ ግቢ ውስጥ ቅዱስ በሆነ ስፍራ ይበላል።+ ዘሌዋውያን 10:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 እንዲሁም የሚወዘወዘውን መባ ፍርምባና የቅዱሱን ድርሻ+ እግር አንተም ሆንክ ከአንተ ጋር ያሉት ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ንጹሕ በሆነ ስፍራ ትበሉታላችሁ፤+ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች እስራኤላውያን ከሚያቀርቧቸው የኅብረት መሥዋዕቶች ላይ የአንተ ድርሻና የወንዶች ልጆችህ ድርሻ ሆነው የተሰጡ ናቸው። ዘኁልቁ 18:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 በተጨማሪም ይሖዋ አሮንን እንዲህ አለው፦ “ለእኔ በሚቀርቡት መዋጮዎች+ ላይ እኔ ራሴ ኃላፊ አድርጌ ሾሜሃለሁ። እስራኤላውያን የሚያዋጧቸውን ቅዱስ ነገሮች ሁሉ ለአንተና ለወንዶች ልጆችህ ድርሻችሁ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ፤ ይህም ቋሚ ድርሻችሁ ነው።+
25 “አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እንዲህ በላቸው፦ ‘የኃጢአት መባ ሕግ ይህ ነው፦+ ለኃጢአት መባ የሚሆነውም እንስሳ፣ ለሚቃጠል መባ የሚሆነው እንስሳ በሚታረድበት ቦታ+ በይሖዋ ፊት ይታረዳል። ይህ እጅግ ቅዱስ የሆነ ነገር ነው። 26 ይህን ለኃጢአት መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርበው ካህን ይበላዋል።+ በመገናኛ ድንኳኑ ግቢ ውስጥ ቅዱስ በሆነ ስፍራ ይበላል።+
14 እንዲሁም የሚወዘወዘውን መባ ፍርምባና የቅዱሱን ድርሻ+ እግር አንተም ሆንክ ከአንተ ጋር ያሉት ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ንጹሕ በሆነ ስፍራ ትበሉታላችሁ፤+ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች እስራኤላውያን ከሚያቀርቧቸው የኅብረት መሥዋዕቶች ላይ የአንተ ድርሻና የወንዶች ልጆችህ ድርሻ ሆነው የተሰጡ ናቸው።
8 በተጨማሪም ይሖዋ አሮንን እንዲህ አለው፦ “ለእኔ በሚቀርቡት መዋጮዎች+ ላይ እኔ ራሴ ኃላፊ አድርጌ ሾሜሃለሁ። እስራኤላውያን የሚያዋጧቸውን ቅዱስ ነገሮች ሁሉ ለአንተና ለወንዶች ልጆችህ ድርሻችሁ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ፤ ይህም ቋሚ ድርሻችሁ ነው።+