ዘፀአት 29:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 “አሮንንና ወንዶች ልጆቹን ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ+ ታቀርባቸዋለህ፤ በውኃም ታጥባቸዋለህ።+ ዘፀአት 29:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 የቅብዓት ዘይቱንም+ ወስደህ በራሱ ላይ በማፍሰስ ትቀባዋለህ።+ ዘፀአት 30:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 አንተም አሮንንና ወንዶች ልጆቹን ትቀባቸዋለህ፤+ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝም+ ትቀድሳቸዋለህ። ዘፀአት 40:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 አሮንንም ቅዱስ የሆኑትን ልብሶች ካለበስከው+ በኋላ ቀባው፤+ እንዲሁም ቀድሰው፤ እሱም ካህን ሆኖ ያገለግለኛል። ዘሌዋውያን 21:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 “‘ከወንድሞቹ መካከል ሊቀ ካህናት በመሆን በራሱ ላይ የቅብዓት ዘይት የሚፈስበትና+ የክህነት ልብሶቹን እንዲለብስ+ የተሾመው* ካህን ፀጉሩን ማንጨብረር ወይም ልብሶቹን መቅደድ የለበትም።+ መዝሙር 133:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 በራስ ላይ ፈስሶ እስከ ጢም እንደሚዘልቅ፣በአሮን ጢም+ ላይ እንደሚወርድ፣እስከ ልብሱ ኮሌታ ድረስ እንደሚፈስጥሩ ዘይት ነው።+
10 “‘ከወንድሞቹ መካከል ሊቀ ካህናት በመሆን በራሱ ላይ የቅብዓት ዘይት የሚፈስበትና+ የክህነት ልብሶቹን እንዲለብስ+ የተሾመው* ካህን ፀጉሩን ማንጨብረር ወይም ልብሶቹን መቅደድ የለበትም።+