34 እስራኤላውያን ከሚያቀርቧቸው የኅብረት መሥዋዕቶች ላይ የሚወዘወዘውን መባ ፍርምባና የተቀደሰ ድርሻ ሆኖ የቀረበውን እግር እወስዳለሁ፤ ለእስራኤላውያንም ዘላቂ ሥርዓት እንዲሆን ለካህኑ ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ እሰጣቸዋለሁ።+
35 “‘ካህናት ሆነው ይሖዋን ለማገልገል በሚቀርቡበት ቀን፣ ለይሖዋ በእሳት ከቀረቡት መባዎች ላይ ለካህናቱ ይኸውም ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ የሚመደብላቸው ድርሻ ይህ ነው።+