27 ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ የክህነት ሹመት ሥርዓት ከቀረበው አውራ በግ+ ተወስዶ ለሚወዘወዝ መባ የቀረበውን ፍርምባና የተቀደሰ ድርሻ እንዲሆን የተወዘወዘውን እግር ትቀድሳቸዋለህ። 28 ይህም የተቀደሰ ድርሻ ስለሆነ የአሮንና የወንዶች ልጆቹ ይሆናል፤ ይህም እስራኤላውያን የሚፈጽሙት ዘላለማዊ ሥርዓት ነው፤ ይህ ድርሻ እስራኤላውያን የሚያቀርቡት የተቀደሰ ድርሻ ይሆናል።+ ከሚያቀርቧቸው የኅብረት መሥዋዕቶች ላይ ለይሖዋ የሚሰጥ የተቀደሰ ድርሻቸው ነው።+