ዘዳግም 24:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 “የሥጋ ደዌ* ቢከሰት ሌዋውያን ካህናት የሚሰጧችሁን መመሪያዎች ሁሉ በጥንቃቄ ተከተሉ።+ እኔ የሰጠኋቸውንም ትእዛዝ በጥንቃቄ ፈጽሙ። ሚልክያስ 2:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ካህኑ ምንጊዜም በከንፈሮቹ ላይ እውቀት ሊኖረው ይገባል፤ ሰዎችም ሕጉን* ከአፉ ሊሹ ይገባል፤+ ምክንያቱም እሱ የሠራዊት ጌታ የይሖዋ መልእክተኛ ነው።