-
ዘሌዋውያን 14:15-18አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
15 ካህኑም ከአንዱ የሎግ መስፈሪያ ዘይት+ ላይ የተወሰነውን በራሱ የግራ እጅ መዳፍ ላይ ያንቆረቁረዋል። 16 ከዚያም የቀኝ እጁን ጣት በግራ እጁ መዳፍ ላይ ባለው ዘይት ውስጥ ይነክራል፤ ከዘይቱም የተወሰነውን በይሖዋ ፊት ሰባት ጊዜ በጣቱ ይረጨዋል። 17 በእጁም መዳፍ ላይ ከቀረው ዘይት ላይ የተወሰነውን ወስዶ ራሱን የሚያነጻውን ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ የቀኝ እጁን አውራ ጣት እንዲሁም የቀኝ እግሩን አውራ ጣት ይቀባል፤ በበደል መባው ደም ላይ ደርቦ ይቀባዋል። 18 ካህኑም በእጁ መዳፍ ላይ የቀረውን ዘይት ራሱን በሚያነጻው ሰው ራስ ላይ ያፈሰዋል፤ ለሰውየውም በይሖዋ ፊት ያስተሰርይለታል።+
-