13 “‘እንግዲህ ናዝራዊን በተመለከተ ሕጉ ይህ ነው፦ ናዝራዊ ሆኖ የሚቆይበትን ጊዜ ሲያጠናቅቅ+ ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ እንዲመጣ ይደረግ። 14 በዚያም የሚከተሉትን ለይሖዋ መባ አድርጎ ያቅርብ፦ ለሚቃጠል መባ አንድ ዓመት ገደማ የሆነውን እንከን የሌለበት አንድ የበግ ጠቦት፣+ ለኃጢአት መባ አንድ ዓመት ገደማ የሆናትን እንከን የሌለባት አንዲት ጠቦት፣+ ለኅብረት መሥዋዕት እንከን የሌለበትን አንድ አውራ በግ፣+