-
ዘሌዋውያን 14:3, 4አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 ካህኑ ከሰፈሩ ውጭ ወጥቶ ሰውየውን ይመረምረዋል። የሥጋ ደዌ ይዞት የነበረው ሰው ከሥጋ ደዌው ከዳነ 4 ካህኑ ሰውየው ራሱን ለማንጻት በሕይወት ያሉ ሁለት ንጹሕ ወፎችን፣ የአርዘ ሊባኖስ እንጨት፣ ደማቅ ቀይ ማግና ሂሶጵ እንዲያመጣ ያዘዋል።+
-
-
ዘኁልቁ 19:6, 7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 ካህኑም የአርዘ ሊባኖስ እንጨት፣ ሂሶጵና+ ደማቅ ቀይ ማግ ወስዶ ላሟ የምትቃጠልበት እሳት ውስጥ ይጨምራል። 7 ከዚያም ካህኑ ልብሶቹን በውኃ ያጥባል፤ ገላውንም ይታጠባል፤ ከዚያ በኋላ ወደ ሰፈሩ መግባት ይችላል፤ ሆኖም ካህኑ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።
-