ዘሌዋውያን 23:27, 28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 “ሆኖም የዚህ የሰባተኛው ወር አሥረኛ ቀን የስርየት ቀን ነው።+ ቅዱስ ጉባኤ አክብሩ፣ ራሳችሁን አጎሳቁሉ*+ እንዲሁም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ አቅርቡ። 28 ይህ ቀን በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ለእናንተ ማስተሰረያ+ የሚቀርብበት የስርየት ቀን ስለሆነ በዚህ ቀን ምንም ዓይነት ሥራ መሥራት የለባችሁም። ዘኁልቁ 29:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 “‘በዚሁ በሰባተኛው ወር በአሥረኛው ቀን ቅዱስ ጉባኤ አድርጉ፤+ ራሳችሁን አጎሳቁሉ።* ምንም ዓይነት ሥራ አትሥሩ።+
27 “ሆኖም የዚህ የሰባተኛው ወር አሥረኛ ቀን የስርየት ቀን ነው።+ ቅዱስ ጉባኤ አክብሩ፣ ራሳችሁን አጎሳቁሉ*+ እንዲሁም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ አቅርቡ። 28 ይህ ቀን በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ለእናንተ ማስተሰረያ+ የሚቀርብበት የስርየት ቀን ስለሆነ በዚህ ቀን ምንም ዓይነት ሥራ መሥራት የለባችሁም።