ዘሌዋውያን 16:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 በዚህ ቀን፣ ንጹሕ መሆናችሁን ለማሳወቅ ለእናንተ ማስተሰረያ+ ይቀርባል። በይሖዋም ፊት ከኃጢአታችሁ ሁሉ ንጹሕ ትሆናላችሁ።+ ዘሌዋውያን 23:27, 28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 “ሆኖም የዚህ የሰባተኛው ወር አሥረኛ ቀን የስርየት ቀን ነው።+ ቅዱስ ጉባኤ አክብሩ፣ ራሳችሁን አጎሳቁሉ*+ እንዲሁም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ አቅርቡ። 28 ይህ ቀን በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ለእናንተ ማስተሰረያ+ የሚቀርብበት የስርየት ቀን ስለሆነ በዚህ ቀን ምንም ዓይነት ሥራ መሥራት የለባችሁም።
27 “ሆኖም የዚህ የሰባተኛው ወር አሥረኛ ቀን የስርየት ቀን ነው።+ ቅዱስ ጉባኤ አክብሩ፣ ራሳችሁን አጎሳቁሉ*+ እንዲሁም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ አቅርቡ። 28 ይህ ቀን በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ለእናንተ ማስተሰረያ+ የሚቀርብበት የስርየት ቀን ስለሆነ በዚህ ቀን ምንም ዓይነት ሥራ መሥራት የለባችሁም።