-
ሩት 4:4-6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 ስለዚህ ጉዳዩን ለአንተ ላሳውቅህና እንዲህ ልልህ አሰብኩ፦ ‘እዚህ በተሰበሰቡት ነዋሪዎችና በአገሬ ሽማግሌዎች ፊት ግዛው።+ ልትቤዠው የምትፈልግ ከሆነ ተቤዠው። ልትቤዠው የማትፈልግ ከሆነ ግን ንገረኝና ልወቀው፤ ምክንያቱም በቅድሚያ የመቤዠት መብት ያለህ አንተ ነህ፤ እኔ ደግሞ ከአንተ ቀጥሎ ነኝ።’” ሰውየውም “ልቤዠው ፈቃደኛ ነኝ” አለ።+ 5 ከዚያም ቦዔዝ “መሬቱን ከናኦሚ በምትገዛበት ቀን ውርሱ በሟቹ ስም እንዲጠራ ለማድረግ የሟቹ ሚስት ከሆነችው ከሞዓባዊቷ ሩት ላይም መግዛት እንዳለብህ እወቅ” አለው።+ 6 የሚቤዠውም ሰው “የገዛ ርስቴን አደጋ ላይ ልጥል ስለምችል ልቤዠው አልችልም። እኔ ልቤዠው ስለማልችል በእኔ የመቤዠት መብት ተጠቅመህ አንተ ለራስህ ተቤዠው” አለው።
-