ዘፀአት 22:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 “የባዕድ አገር ሰውን አትበድል ወይም አትጨቁን፤+ ምክንያቱም እናንተ ራሳችሁ በግብፅ ምድር ሳላችሁ የባዕድ አገር ሰው ነበራችሁ።+ ዘፀአት 23:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 “የባዕድ አገር ሰውን አትጨቁን። እናንተ ራሳችሁ በግብፅ ምድር ሳላችሁ የባዕድ አገር ሰው ስለነበራችሁ የባዕድ አገር ሰው መሆን ምን ስሜት እንደሚያሳድር* ታውቃላችሁ።+ ዘሌዋውያን 19:34 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 አብሯችሁ የሚኖረውን የባዕድ አገር ሰው እንደ አገራችሁ ተወላጅ አድርጋችሁ ተመልከቱት፤+ እንደ ራሳችሁ አድርጋችሁም ውደዱት፤ ምክንያቱም እናንተም በግብፅ ምድር ሳላችሁ የባዕድ አገር ሰው ነበራችሁ።+ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። ዘዳግም 10:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 አባት ለሌለው* ልጅና ለመበለት ይፈርዳል፤+ እንዲሁም የባዕድ አገሩን ሰው ይወደዋል፤+ ምግብና ልብስም ይሰጠዋል።
9 “የባዕድ አገር ሰውን አትጨቁን። እናንተ ራሳችሁ በግብፅ ምድር ሳላችሁ የባዕድ አገር ሰው ስለነበራችሁ የባዕድ አገር ሰው መሆን ምን ስሜት እንደሚያሳድር* ታውቃላችሁ።+
34 አብሯችሁ የሚኖረውን የባዕድ አገር ሰው እንደ አገራችሁ ተወላጅ አድርጋችሁ ተመልከቱት፤+ እንደ ራሳችሁ አድርጋችሁም ውደዱት፤ ምክንያቱም እናንተም በግብፅ ምድር ሳላችሁ የባዕድ አገር ሰው ነበራችሁ።+ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።