ዘዳግም 28:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 “ይሖዋ በአንተ ላይ የሚነሱ ጠላቶችህ በፊትህ ድል እንዲሆኑ ያደርጋል።+ ከአንድ አቅጣጫ ጥቃት ይሰነዝሩብሃል፤ ሆኖም በሰባት አቅጣጫ ከፊትህ ይሸሻሉ።+ ኢያሱ 23:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 አምላካችሁ ይሖዋ በገባላችሁ ቃል መሠረት+ ለእናንተ ስለሚዋጋላችሁ+ ከእናንተ አንዱ፣ ሺህ ሰው ያሳድዳል።+ መሳፍንት 7:15, 16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ጌድዮንም ሕልሙንና ፍቺውን ሲሰማ ለአምላክ ሰገደ።+ ከዚያም ወደ እስራኤላውያን ሰፈር ተመልሶ “ተነሱ፤ ይሖዋ የምድያማውያንን ሰፈር በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቷችኋል” አላቸው። 16 በመቀጠልም 300ዎቹን ሰዎች በሦስት ቡድን ከፈላቸው፤ ለሁሉም ቀንደ መለከትና+ በውስጣቸው ችቦ ያለባቸው ትላልቅ ባዶ ማሰሮዎች ሰጣቸው። መሳፍንት 15:15, 16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 እሱም በቅርቡ የሞተ የአንድ አህያ መንጋጋ አገኘ፤ መንጋጋውንም አንስቶ በእሱ 1,000 ሰው ገደለ።+ 16 ከዚያም ሳምሶን እንዲህ አለ፦ “በአህያ መንጋጋ በክምር ላይ ክምር አነባባሪ፤ በአህያ መንጋጋ 1,000 ሰው ዘራሪ!”+ 1 ዜና መዋዕል 11:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 የኢዮዓብ+ ወንድም አቢሳ+ የሌሎች ሦስት ሰዎች መሪ ነበር፤ እሱም ጦሩን ሰብቆ 300 ሰው ገደለ፤ እንደ ሦስቱም ሰዎች ዝነኛ ነበር።+
15 ጌድዮንም ሕልሙንና ፍቺውን ሲሰማ ለአምላክ ሰገደ።+ ከዚያም ወደ እስራኤላውያን ሰፈር ተመልሶ “ተነሱ፤ ይሖዋ የምድያማውያንን ሰፈር በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቷችኋል” አላቸው። 16 በመቀጠልም 300ዎቹን ሰዎች በሦስት ቡድን ከፈላቸው፤ ለሁሉም ቀንደ መለከትና+ በውስጣቸው ችቦ ያለባቸው ትላልቅ ባዶ ማሰሮዎች ሰጣቸው።
15 እሱም በቅርቡ የሞተ የአንድ አህያ መንጋጋ አገኘ፤ መንጋጋውንም አንስቶ በእሱ 1,000 ሰው ገደለ።+ 16 ከዚያም ሳምሶን እንዲህ አለ፦ “በአህያ መንጋጋ በክምር ላይ ክምር አነባባሪ፤ በአህያ መንጋጋ 1,000 ሰው ዘራሪ!”+