-
ኢሳይያስ 9:20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 አንዱ በቀኝ በኩል ይቆርጣል፤
ሆኖም ይራባል፤
ሌላው ደግሞ በግራ በኩል ይበላል፤
ሆኖም አይጠግብም።
እያንዳንዳቸው የገዛ ክንዳቸውን ሥጋ ይበላሉ፤
-
ሚክያስ 6:14አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 ትበላለህ፤ ግን አትጠግብም፤
ሆድህም ባዶ ይሆናል።+
የምትወስዳቸውን ነገሮች ጠብቀህ ማቆየት አትችልም፤
ጠብቀህ ያቆየኸውንም ነገር ሁሉ ለሰይፍ አሳልፌ እሰጠዋለሁ።
-
-
ሐጌ 1:6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 ብዙ ዘር ዘራችሁ፤ የምትሰበስቡት ግን ጥቂት ነው።+ ትበላላችሁ፤ ሆኖም አትጠግቡም። ትጠጣላችሁ፤ ሆኖም አትረኩም። ትለብሳላችሁ፤ የሚሞቀው ሰው ግን የለም። ተቀጥሮ የሚሠራው ደሞዙን ብዙ ቀዳዳዎች ባሉት ከረጢት ውስጥ ያስቀምጣል።’”
-
-
-