ዘዳግም 4:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ መሐሪ አምላክ ነው።+ አይተውህም፣ አያጠፋህም ወይም ለአባቶችህ በመሐላ ያጸናላቸውን ቃል ኪዳን አይረሳም።+ 2 ነገሥት 13:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ሆኖም ይሖዋ ከአብርሃም፣+ ከይስሐቅና+ ከያዕቆብ+ ጋር ስለገባው ቃል ኪዳን ሲል ሞገስና አሳቢነት አሳያቸው፤ ምሕረትም አደረገላቸው።+ ሊያጠፋቸው አልፈለገም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ከፊቱ አላስወገዳቸውም። ነህምያ 9:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 ከታላቅ ምሕረትህ የተነሳ ፈጽመህ አላጠፋሃቸውም+ ወይም አልተውካቸውም፤ ምክንያቱም አንተ ሩኅሩኅና* መሐሪ አምላክ ነህ።+
23 ሆኖም ይሖዋ ከአብርሃም፣+ ከይስሐቅና+ ከያዕቆብ+ ጋር ስለገባው ቃል ኪዳን ሲል ሞገስና አሳቢነት አሳያቸው፤ ምሕረትም አደረገላቸው።+ ሊያጠፋቸው አልፈለገም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ከፊቱ አላስወገዳቸውም።