-
ዘሌዋውያን 1:15-17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
15 ካህኑም በመሠዊያው ላይ ያቀርበዋል፤ እንዲሁም አንገቱ ላይ ቦጭቆ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ ያደርገዋል። ደሙ ግን በመሠዊያው ጎን ይንጠፍጠፍ። 16 ቋቱንና ላባዎቹንም ከለየ በኋላ ከመሠዊያው አጠገብ በስተ ምሥራቅ በኩል ወዳለው አመድ* ወደሚደፋበት ቦታ ይወርውራቸው።+ 17 ሙሉ በሙሉ ለሁለት ሳይለያየው ክንፎቹን ይዞ ይሰነጥቀዋል። ከዚያም ካህኑ በመሠዊያው ላይ ይኸውም በእሳቱ ላይ ባለው እንጨት ላይ እንዲጨስ ያደርገዋል። ይህም የሚቃጠል መባ ማለትም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ ነው።
-