ዘፀአት 13:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 “ከእስራኤል ሕዝብ መካከል በኩር የሆነውን ወንድ ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ።* ከሰውም ሆነ ከእንስሳ መካከል በኩር የሆነው ወንድ ሁሉ* የእኔ ነው።”+ ዘፀአት 34:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 “በኩር የሆነ ወንድ ሁሉ* የእኔ ነው፤+ ደግሞም የመንጋህ በኩር ሁሉ፣ በኩር የሆነ በሬም ሆነ ተባዕት በግ የእኔ ነው።+ ዘኁልቁ 18:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 “ከሰውም ሆነ ከእንስሳ ለይሖዋ የሚያቀርቡት የእያንዳንዱ ሕይወት ያለው ነገር* በኩር ሁሉ+ የአንተ መሆን ይኖርበታል። ሆኖም ከሰው በኩር የሆነውን ሁሉ መዋጀት ይኖርብሃል፤+ እንዲሁም ርኩስ ከሆነ እንስሳ በኩር የሆነውን ሁሉ መዋጀት ይገባሃል።+ ሉቃስ 2:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ይህን ያደረጉት “በኩር የሆነ ወንድ ሁሉ* ለይሖዋ* የተቀደሰ መሆን አለበት”+ ተብሎ በይሖዋ* ሕግ ላይ በተጻፈው መሠረት ነው።
15 “ከሰውም ሆነ ከእንስሳ ለይሖዋ የሚያቀርቡት የእያንዳንዱ ሕይወት ያለው ነገር* በኩር ሁሉ+ የአንተ መሆን ይኖርበታል። ሆኖም ከሰው በኩር የሆነውን ሁሉ መዋጀት ይኖርብሃል፤+ እንዲሁም ርኩስ ከሆነ እንስሳ በኩር የሆነውን ሁሉ መዋጀት ይገባሃል።+