3 ሆኖም የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የጊልያድ ልጅ፣ የሄፌር ልጅ ሰለጰአድ+ ሴቶች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ የሴቶች ልጆቹም ስም ማህላ፣ ኖኅ፣ ሆግላ፣ ሚልካ እና ቲርጻ ነበር። 4 እነሱም ወደ ካህኑ አልዓዛር፣+ ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱና ወደ አለቆቹ ቀርበው “ይሖዋ በወንድሞቻችን መካከል ርስት እንዲሰጠን ሙሴን አዞት ነበር” አሏቸው።+ ስለዚህ ኢያሱ ይሖዋ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት በአባታቸው ወንድሞች መካከል ርስት ሰጣቸው።+