ዘፀአት 34:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 “የሳምንታት በዓልህን መጀመሪያ በደረሰው የስንዴ በኩር አክብር፤ የአዝመራ መክተቻን በዓልም* በዓመቱ ማብቂያ ላይ አክብር።+ ዘዳግም 16:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ከዚያም አምላክህ ይሖዋ በባረከህ መጠን+ በምታቀርበው የፈቃደኝነት መባ አማካኝነት ለአምላክህ ለይሖዋ የሳምንታት በዓልን ታከብራለህ።+ የሐዋርያት ሥራ 2:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 በጴንጤቆስጤ* በዓል ቀን+ ሁሉም በአንድ ቦታ ተሰብስበው ነበር።