-
ዘኁልቁ 28:11-13አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 “‘በየወሩም* መባቻ ላይ ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግ እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው እንከን የሌለባቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ለይሖዋ የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤+ 12 ለእያንዳንዱ ወይፈን ሦስት አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ+ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ ለአውራው በግ ደግሞ ሁለት አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤+ 13 ለእያንዳንዱም ተባዕት የበግ ጠቦት አንድ አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ ይኸውም ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ የሚቃጠል መባ+ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ።
-