-
ዘኁልቁ 4:24-26አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
24 የጌድሶናውያን ቤተሰቦች እንዲንከባከቡና እንዲሸከሙ+ የተመደቡት እነዚህን ነገሮች ነው፦ 25 እነሱም የማደሪያ ድንኳኑን የድንኳን ጨርቆች፣+ የመገናኛ ድንኳኑን ጨርቆች፣ መደረቢያውንና ከእሱ በላይ ያለውን ከአቆስጣ ቆዳ የተሠራ መደረቢያ+ እንዲሁም የመገናኛ ድንኳኑን መግቢያ መከለያ*+ ይሸከማሉ፤ 26 በተጨማሪም የግቢውን መጋረጃዎች፣+ በማደሪያ ድንኳኑና በመሠዊያው ዙሪያ ባለው ግቢ መግቢያ ላይ የሚገኘውን መከለያ፣*+ የድንኳን ገመዶቻቸውንና ዕቃዎቻቸውን በሙሉ እንዲሁም ለአገልግሎቱ የሚውሉትን ነገሮች ሁሉ ይሸከማሉ። የሥራ ምድባቸው ይህ ነው።
-