19 ንጹሕ የሆነውም ሰው ውኃውን በረከሰው ሰው ላይ በሦስተኛው ቀንና በሰባተኛው ቀን ላይ ይረጨዋል፤ በሰባተኛውም ቀን ከኃጢአት ያነጻዋል፤+ ከዚያም ሰውየው ልብሶቹን ይጠብ፤ በውኃም ይታጠብ፤ ማታም ላይ ንጹሕ ይሆናል።
20 “‘ሆኖም የረከሰውና ራሱን ያላነጻው ሰው የይሖዋን መቅደስ ስላረከሰ ይህ ሰው ከጉባኤው መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ መደረግ አለበት።+ የሚያነጻው ውኃ ስላልተረጨበት ሰውየው ርኩስ ነው።