7 ሙሴ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ በባሳን ርስት ሰጥቶ ነበር፤+ ኢያሱ ደግሞ ለቀረው የነገዱ እኩሌታ ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ ከወንድሞቻቸው ጋር መሬት ሰጣቸው።+ በተጨማሪም ኢያሱ ወደ ድንኳኖቻቸው እንዲሄዱ ባሰናበታቸው ጊዜ ባረካቸው፤ 8 እንዲህም አላቸው፦ “ብዙ ሀብት፣ እጅግ ብዙ ከብት፣ ብር፣ ወርቅ፣ መዳብ፣ ብረትና እጅግ ብዙ ልብስ ይዛችሁ ወደየድንኳኖቻችሁ ተመለሱ።+ ከጠላቶቻችሁ ያገኛችሁትን ምርኮ ወስዳችሁ ከወንድሞቻችሁ ጋር ተካፈሉ።”+