12 ኢያሱም ለሮቤላውያን፣ ለጋዳውያንና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ እንዲህ አላቸው፦ 13 “የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ እንዲህ በማለት ያዘዛችሁን ቃል አስታውሱ፦+ ‘አምላካችሁ ይሖዋ እረፍት ሰጥቷችኋል፤ ይህን ምድር አውርሷችኋል። 14 ሚስቶቻችሁ፣ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ ሙሴ በሰጣችሁ ከዮርዳኖስ ወዲህ ባለው ምድር ላይ ይቀመጣሉ፤+ ሆኖም ብርቱ የሆናችሁት ተዋጊዎች በሙሉ+ የጦርነት አሰላለፍ በመከተል ወንድሞቻችሁን ቀድማችሁ ትሻገራላችሁ።+ እነሱን መርዳት ይገባችኋል፤