-
ኢያሱ 12:1, 2አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 እንግዲህ እስራኤላውያን ድል ያደረጓቸውና ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ የሚገኘውን ምድራቸውን ይኸውም ከአርኖን ሸለቆ*+ አንስቶ እስከ ሄርሞን ተራራ+ ድረስ ያለውን እንዲሁም በስተ ምሥራቅ የሚገኘውን አረባን በሙሉ የወረሱባቸው ነገሥታት እነዚህ ናቸው፦+ 2 በሃሽቦን የሚኖረውና በአርኖን ሸለቆ* ዳርቻ ላይ በምትገኘው በአሮዔር+ ሆኖ የሚገዛው የአሞራውያን ንጉሥ ሲሖን፤+ እሱም በአርኖን ሸለቆ+ መሃል ካለው ስፍራ አንስቶ የአሞናውያን ወሰን እስከሆነው እስከ ያቦቅ ሸለቆ* ድረስ ያለውን የጊልያድን እኩሌታ ይገዛ ነበር።
-