ዘፀአት 23:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ለአማልክታቸው አትስገድ፤ ወይም ተታለህ እነሱን አታገልግል፤ የሚያደርጉትን ነገር አታድርግ።+ ከዚህ ይልቅ አውድማቸው፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውንም ሰባብር።+ ዘፀአት 34:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ከዚህ ይልቅ መሠዊያዎቻቸውን ታፈራርሳላችሁ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን ትሰባብራላችሁ፤ እንዲሁም የማምለኪያ ግንዶቻቸውን* ትቆራርጣላችሁ።+ ዘፀአት 34:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 “ከቀለጠ ብረት አማልክት አትሥራ።+ ዘዳግም 7:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 “ከዚህ ይልቅ እንዲህ አድርጉባቸው፦ መሠዊያዎቻቸውን አፈራርሱ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን ሰባብሩ፤+ የማምለኪያ ግንዶቻቸውን* ቆራርጡ፤+ የተቀረጹ ምስሎቻቸውንም በእሳት አቃጥሉ።+ ዘዳግም 12:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 መሠዊያዎቻቸውን አፈራርሱ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን አድቅቁ፤+ የማምለኪያ ግንዶቻቸውንም* በእሳት አቃጥሉ፤ የአማልክታቸውን የተቀረጹ ምስሎች ሰባብራችሁ ጣሉ፤+ ስማቸውንም ከዚያ ስፍራ ሙሉ በሙሉ ደምስሱ።+
5 “ከዚህ ይልቅ እንዲህ አድርጉባቸው፦ መሠዊያዎቻቸውን አፈራርሱ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን ሰባብሩ፤+ የማምለኪያ ግንዶቻቸውን* ቆራርጡ፤+ የተቀረጹ ምስሎቻቸውንም በእሳት አቃጥሉ።+
3 መሠዊያዎቻቸውን አፈራርሱ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን አድቅቁ፤+ የማምለኪያ ግንዶቻቸውንም* በእሳት አቃጥሉ፤ የአማልክታቸውን የተቀረጹ ምስሎች ሰባብራችሁ ጣሉ፤+ ስማቸውንም ከዚያ ስፍራ ሙሉ በሙሉ ደምስሱ።+