ዘፀአት 23:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 “ወሰንህንም ከቀይ ባሕር አንስቶ እስከ ፍልስጤማውያን ባሕር እንዲሁም ከምድረ በዳው አንስቶ እስከ ወንዙ* ድረስ አደርገዋለሁ።+ ምክንያቱም የምድሩን ነዋሪዎች በእጃችሁ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ አንተም ከፊትህ አባረህ ታስወጣቸዋለህ።+ ኢያሱ 15:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ለይሁዳ ነገድ ለየቤተሰቡ በዕጣ የተሰጠው ርስት+ እስከ ኤዶም+ ይኸውም እስከ ጺን ምድረ በዳና እስከ ኔጌብ ደቡባዊ ጫፍ ድረስ ይዘልቃል። ኢያሱ 15:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ከዚያም ወደ አጽሞን+ ይዘልቅና ወደ ግብፅ ሸለቆ*+ ይቀጥላል፤ ወሰኑም ባሕሩ* ጋ ሲደርስ ያበቃል። ደቡባዊ ወሰናቸው ይህ ነበር።
31 “ወሰንህንም ከቀይ ባሕር አንስቶ እስከ ፍልስጤማውያን ባሕር እንዲሁም ከምድረ በዳው አንስቶ እስከ ወንዙ* ድረስ አደርገዋለሁ።+ ምክንያቱም የምድሩን ነዋሪዎች በእጃችሁ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ አንተም ከፊትህ አባረህ ታስወጣቸዋለህ።+