ዘፍጥረት 9:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ከዚህም በተጨማሪ ሕይወታችሁ የሆነውን ደማችሁን* የሚያፈሰውን ሁሉ ተጠያቂ አደርገዋለሁ። እያንዳንዱን ሕያው ፍጡር ተጠያቂ አደርገዋለሁ፤ እያንዳንዱንም ሰው ለወንድሙ ሕይወት ተጠያቂ አደርገዋለሁ።+ ዘፀአት 21:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 “አንድ ሰው ሌላውን ሰው መትቶ ቢገድል ገዳዩ ይገደል።+ ዘሌዋውያን 24:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 “‘አንድ ሰው የሰው ሕይወት ካጠፋ* ይገደል።+ ዘዳግም 19:11, 12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 “ይሁን እንጂ አንድ ሰው ባልንጀራውን ቢጠላው፣+ አድብቶም ለሞት የሚያበቃ ጉዳት ቢያደርስበትና ሰውየው ቢሞት፣ ገዳዩም ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ ቢሸሽ 12 የሚኖርበት ከተማ ሽማግሌዎች ሰውየውን ከዚያ በማስመጣት ለደም ተበቃዩ አሳልፈው ይስጡት፤ ይህ ሰው ሞት ይገባዋል።+
5 ከዚህም በተጨማሪ ሕይወታችሁ የሆነውን ደማችሁን* የሚያፈሰውን ሁሉ ተጠያቂ አደርገዋለሁ። እያንዳንዱን ሕያው ፍጡር ተጠያቂ አደርገዋለሁ፤ እያንዳንዱንም ሰው ለወንድሙ ሕይወት ተጠያቂ አደርገዋለሁ።+
11 “ይሁን እንጂ አንድ ሰው ባልንጀራውን ቢጠላው፣+ አድብቶም ለሞት የሚያበቃ ጉዳት ቢያደርስበትና ሰውየው ቢሞት፣ ገዳዩም ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ ቢሸሽ 12 የሚኖርበት ከተማ ሽማግሌዎች ሰውየውን ከዚያ በማስመጣት ለደም ተበቃዩ አሳልፈው ይስጡት፤ ይህ ሰው ሞት ይገባዋል።+