-
ዘኁልቁ 4:31-33አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
31 በመገናኛ ድንኳኑ ከሚያከናውኑት አገልግሎት ጋር በተያያዘ የሚከተሉትን ነገሮች የመሸከም ኃላፊነት+ ተጥሎባቸዋል፦ የማደሪያ ድንኳኑን ቋሚዎች፣+ አግዳሚ እንጨቶቹን፣+ ዓምዶቹን፣+ መሰኪያዎቹን፣+ 32 በግቢው ዙሪያ ያሉትን ቋሚዎች፣+ መሰኪያዎቻቸውን፣+ የድንኳን ካስማዎቻቸውን፣+ የድንኳን ገመዶቻቸውን እንዲሁም ቁሳቁሶቻቸውንና ከዚህ አገልግሎት ጋር የተያያዙትን ነገሮች ሁሉ ይሸከማሉ። በኃላፊነት የሚሸከሙትንም ዕቃ በስም ጠቅሰህ ትመድብላቸዋለህ። 33 የሜራሪ ወንዶች ልጆች ቤተሰቦች+ በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር አመራር ሥር ሆነው በመገናኛ ድንኳኑ የሚያገለግሉት በዚህ መሠረት ነው።”+
-