ዘፍጥረት 29:34 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 አሁንም ደግሞ ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። እሷም “ሦስት ወንዶች ልጆች ስለወለድኩለት አሁን ባሌ ይቀርበኛል” አለች። በዚህም የተነሳ ሌዊ*+ ተባለ። ዘፍጥረት 46:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 የሌዊ+ ወንዶች ልጆች ጌድሶን፣ ቀአት እና ሜራሪ ነበሩ።+ ዘኁልቁ 3:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 “በእስራኤላውያን በኩሮች ሁሉ* ምትክ ሌዋውያኑን ከእስራኤላውያን መካከል እወስዳለሁ፤+ ሌዋውያኑም የእኔ ይሆናሉ።