-
ዘኁልቁ 7:13-17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
13 መባውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል*+ መሠረት 130 ሰቅል* የሚመዝን አንድ የብር ሳህንና 70 ሰቅል የሚመዝን አንድ የብር ጎድጓዳ ሳህን ሲሆን እያንዳንዳቸው ለእህል መባ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፤+ 14 እንዲሁም ዕጣን የተሞላ 10 ሰቅል የሚመዝን አንድ የወርቅ ጽዋ፣ 15 ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና አንድ ዓመት ገደማ የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣+ 16 ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ የፍየል ጠቦት+ 17 እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት+ የሚሆኑ ሁለት ከብቶች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ተባዕት ፍየሎችና እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቀረበ። የአሚናዳብ+ ልጅ ነአሶን ያቀረበው መባ ይህ ነበር።
-