6 ካህናቱም ሆኑ የይሖዋን መዝሙር ለማጀብ የሚያገለግሉ የሙዚቃ መሣሪያዎችን የያዙት ሌዋውያን እንዲያገለግሉ በተመደቡበት ስፍራ ቆመው ነበር።+ (ንጉሥ ዳዊት እነዚህን መሣሪያዎች የሠራው ከእነሱ ጋር ሆኖ ውዳሴ በሚያቀርብበት ጊዜ “ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና” በማለት ይሖዋን ለማመስገን ነው።) ካህናቱ በእነሱ ትይዩ ሆነው መለከቶቹን በኃይል ይነፉ ነበር፤+ በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን ሁሉ በዚያ ቆመው ነበር።