ዘኁልቁ 3:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 አሮንንና ወንዶች ልጆቹን ሹማቸው፤ እነሱም የክህነት ኃላፊነታቸውን ይወጡ፤+ ማንኛውም ያልተፈቀደለት ሰው* ወደ መቅደሱ ቢቀርብ ይገደል።”+ ዘኁልቁ 3:38 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 38 በማደሪያ ድንኳኑ ፊት ለፊት በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ ፊት ፀሐይ በምትወጣበት አቅጣጫ የሰፈሩት ሙሴና አሮን እንዲሁም የአሮን ወንዶች ልጆች ነበሩ። እስራኤላውያንን ወክለው እንዲያከናውኑ የተጣለባቸው ግዴታም መቅደሱን የመንከባከብ ኃላፊነት ነበር። ማንኛውም ያልተፈቀደለት ሰው* ወደዚያ ቢቀርብ ይገደላል።+ ዘኁልቁ 16:45 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 45 “በአንዴ እንዳጠፋቸው+ ራሳችሁን ከዚህ ማኅበረሰብ ለዩ።” እነሱም በዚህ ጊዜ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፉ።+
38 በማደሪያ ድንኳኑ ፊት ለፊት በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ ፊት ፀሐይ በምትወጣበት አቅጣጫ የሰፈሩት ሙሴና አሮን እንዲሁም የአሮን ወንዶች ልጆች ነበሩ። እስራኤላውያንን ወክለው እንዲያከናውኑ የተጣለባቸው ግዴታም መቅደሱን የመንከባከብ ኃላፊነት ነበር። ማንኛውም ያልተፈቀደለት ሰው* ወደዚያ ቢቀርብ ይገደላል።+