-
ዘዳግም 18:21, 22አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
21 ሆኖም አንተ በልብህ “ታዲያ ቃሉን ይሖዋ እንዳልተናገረው እንዴት እናውቃለን?” ብለህ ታስብ ይሆናል። 22 ነቢዩ በይሖዋ ስም ቢናገርና የተናገረው ቃል ባይፈጸም ወይም እውነት ሆኖ ባይገኝ ይህን ቃል የተናገረው ይሖዋ አይደለም። ይህ ቃል ነቢዩ በእብሪት ተነሳስቶ የተናገረው ነው። እሱን ልትፈራው አይገባም።’
-