10 “‘ከወንድሞቹ መካከል ሊቀ ካህናት በመሆን በራሱ ላይ የቅብዓት ዘይት የሚፈስበትና+ የክህነት ልብሶቹን እንዲለብስ+ የተሾመው ካህን ፀጉሩን ማንጨብረር ወይም ልብሶቹን መቅደድ የለበትም።+ 11 ወደ ሞተ ሰው አይጠጋ።+ ሌላው ቀርቶ ለአባቱ ወይም ለእናቱ ሲል ራሱን አያርክስ። 12 ለአምላክ የተወሰኑ መሆንን የሚያሳየው ምልክት ይኸውም የአምላኩ የቅብዓት ዘይት+ በላዩ ላይ ስላለ ከመቅደሱ መውጣትም ሆነ የአምላኩን መቅደስ ማርከስ የለበትም።+ እኔ ይሖዋ ነኝ።