-
ኢያሱ 12:4-6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 እንዲሁም በአስታሮትና በኤድራይ ይኖር የነበረውንና ከመጨረሻዎቹ የረፋይም+ ወገኖች አንዱ የሆነውን የባሳንን ንጉሥ የኦግን+ ግዛት፤ 5 እሱም የሄርሞንን ተራራ፣ ሳልካን፣ ባሳንን+ በሙሉ እስከ ገሹራውያንና እስከ ማአካታውያን+ ወሰን ድረስ እንዲሁም እስከ ሃሽቦን+ ንጉሥ እስከ ሲሖን ግዛት ድረስ ያለውን የጊልያድን እኩሌታ ይገዛ ነበር።
6 የይሖዋ አገልጋይ ሙሴና እስራኤላውያን እነዚህን ነገሥታት ድል አደረጓቸው፤+ ከዚያም የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ ምድራቸውን ለሮቤላውያን፣ ለጋዳውያንና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርጎ ሰጠ።+
-