-
ዘኁልቁ 22:23አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
23 አህያዋም የይሖዋ መልአክ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ መንገዱ ላይ መቆሙን ስታይ ከመንገዱ ወጥታ ወደ እርሻ ለመግባት ሞከረች። ሆኖም በለዓም አህያዋን ወደ መንገዱ ለመመለስ ይደበድባት ጀመር።
-
-
ዘኁልቁ 22:25አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
25 አህያዋም የይሖዋን መልአክ ስታይ ግንቡን መታከክ ጀመረች፤ የበለዓምንም እግር ከግንቡ ጋር አጣበቀችው፤ በለዓምም እንደገና ይደበድባት ጀመር።
-
-
ዘኁልቁ 22:27አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
27 አህያዋም የይሖዋን መልአክ ስታይ በለዓም ላይዋ ላይ እንዳለ ተኛች፤ በዚህ ጊዜ በለዓም እጅግ ተቆጣ፤ አህያዋንም በዱላው ይቀጠቅጣት ጀመር።
-