ዘፍጥረት 30:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 በመሆኑም “ይሖዋ ሌላ ወንድ ልጅ ጨመረልኝ” በማለት ስሙን ዮሴፍ*+ አለችው። ዘፍጥረት 35:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ከራሔል የወለዳቸው ወንዶች ልጆቹ ዮሴፍና ቢንያም ነበሩ። ዘፍጥረት 46:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ዮሴፍ በግብፅ ምድር ሳለ ምናሴንና+ ኤፍሬምን*+ ወለደ፤ እነዚህም የኦን* ካህን የሆነው የጶጥፌራ ልጅ አስናት+ የወለደችለት ናቸው።