ዘኁልቁ 32:33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 33 ስለዚህ ሙሴ ለጋድ ልጆችና ለሮቤል ልጆች+ እንዲሁም ለዮሴፍ ልጅ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ+ የአሞራውያንን ንጉሥ የሲሖንን ግዛትና+ የባሳንን ንጉሥ የኦግን ግዛት+ ይኸውም በክልሎቹ ውስጥ የሚገኙ ከተሞች ይዞታ የሆነውን ምድር እንዲሁም በዙሪያው ባለው ምድር ያሉትን ከተሞች ሰጣቸው። ዘዳግም 29:7, 8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 በኋላም ወደዚህ ስፍራ መጣችሁ፤ የሃሽቦን ንጉሥ ሲሖን+ እና የባሳን ንጉሥ ኦግ+ ሊወጉን ወጡ፤ ሆኖም ድል አደረግናቸው።+ 8 ከዚያም ምድራቸውን ወስደን ለሮቤላውያን፣ ለጋዳውያንና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገን ሰጠናቸው።+ ኢያሱ 13:29, 30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 በተጨማሪም ሙሴ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ይኸውም ለግማሹ የምናሴ ነገድ በየቤተሰባቸው ርስት ሰጠ።+ 30 ግዛታቸውም ከማሃናይም+ አንስቶ ያለው ሲሆን ባሳንን በሙሉ፣ የባሳንን ንጉሥ የኦግን ንጉሣዊ ግዛት በሙሉ፣ በባሳን የሚገኙትን የያኢር+ የድንኳን ሰፈሮች በሙሉ፣ 60 ከተሞችን ያጠቃልላል።
33 ስለዚህ ሙሴ ለጋድ ልጆችና ለሮቤል ልጆች+ እንዲሁም ለዮሴፍ ልጅ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ+ የአሞራውያንን ንጉሥ የሲሖንን ግዛትና+ የባሳንን ንጉሥ የኦግን ግዛት+ ይኸውም በክልሎቹ ውስጥ የሚገኙ ከተሞች ይዞታ የሆነውን ምድር እንዲሁም በዙሪያው ባለው ምድር ያሉትን ከተሞች ሰጣቸው።
7 በኋላም ወደዚህ ስፍራ መጣችሁ፤ የሃሽቦን ንጉሥ ሲሖን+ እና የባሳን ንጉሥ ኦግ+ ሊወጉን ወጡ፤ ሆኖም ድል አደረግናቸው።+ 8 ከዚያም ምድራቸውን ወስደን ለሮቤላውያን፣ ለጋዳውያንና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገን ሰጠናቸው።+
29 በተጨማሪም ሙሴ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ይኸውም ለግማሹ የምናሴ ነገድ በየቤተሰባቸው ርስት ሰጠ።+ 30 ግዛታቸውም ከማሃናይም+ አንስቶ ያለው ሲሆን ባሳንን በሙሉ፣ የባሳንን ንጉሥ የኦግን ንጉሣዊ ግዛት በሙሉ፣ በባሳን የሚገኙትን የያኢር+ የድንኳን ሰፈሮች በሙሉ፣ 60 ከተሞችን ያጠቃልላል።