ዘዳግም 17:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 በመንግሥቱ ዙፋን ላይ በሚቀመጥበትም ጊዜ በሌዋውያን ካህናት እጅ ካለው ላይ ወስዶ የዚህን ሕግ ቅጂ ለራሱ በመጽሐፍ* ላይ ይጻፍ።+ 2 ዜና መዋዕል 34:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ወደ ይሖዋ ቤት የመጣውን ገንዘብ በሚያወጡበት+ ጊዜ ካህኑ ኬልቅያስ በሙሴ በኩል* የተሰጠውን+ የይሖዋን ሕግ መጽሐፍ+ አገኘ።