20 ሙሴም እንዲህ አላቸው፦ “ይህን ብታደርጉ ይኸውም በጦርነቱ ለመካፈል በይሖዋ ፊት ታጥቃችሁ ብትነሱ+ 21 እንዲሁም ጠላቶቹን ከፊቱ እስኪያስወግድ ድረስ+ እያንዳንዳችሁ የጦር መሣሪያችሁን ይዛችሁ በይሖዋ ፊት ዮርዳኖስን ብትሻገሩና 22 ምድሪቱ በይሖዋ ፊት እስክትገዛ ድረስ+ በዚያ ብትቆዩ፣ ከዚያ በኋላ መመለስ ትችላላችሁ፤+ በይሖዋም ሆነ በእስራኤላውያን ዘንድ ከበደል ነፃ ትሆናላችሁ። ከዚያም ይህች ምድር በይሖዋ ፊት የእናንተ ርስት ትሆናለች።+