-
ኢያሱ 1:14, 15አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 ሚስቶቻችሁ፣ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ ሙሴ በሰጣችሁ ከዮርዳኖስ ወዲህ ባለው ምድር* ላይ ይቀመጣሉ፤+ ሆኖም ብርቱ የሆናችሁት ተዋጊዎች በሙሉ+ የጦርነት አሰላለፍ በመከተል ወንድሞቻችሁን ቀድማችሁ ትሻገራላችሁ።+ እነሱን መርዳት ይገባችኋል፤ 15 ይሖዋ ለእናንተ እንዳደረገው ሁሉ ለወንድሞቻችሁም እረፍት እስከሚሰጣቸውና አምላካችሁ ይሖዋ የሚሰጣቸውን ምድር እስከሚወርሱ ድረስ ይህን ማድረግ ይኖርባችኋል። ከዚያም እንድትይዟትና እንድትወርሷት ወደተሰጠቻችሁ ይኸውም የይሖዋ አገልጋይ ሙሴ ወደሰጣችሁ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ወደምትገኘው ምድር ትመለሳላችሁ።’”+
-