ዘፀአት 28:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 ኡሪሙንና ቱሚሙን*+ በፍርድ የደረት ኪሱ ውስጥ ታስቀምጣቸዋለህ፤ አሮን በይሖዋ ፊት ለመቅረብ በሚገባበት ጊዜ በልቡ ላይ መሆን አለባቸው፤ አሮን በይሖዋ ፊት በሚቀርብበት ጊዜ ለእስራኤላውያን ፍርድ መስጫውን ዘወትር በልቡ ላይ ይሸከም። ዘሌዋውያን 8:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 በመሆኑም ሙሴ አሮንንና ወንዶች ልጆቹን አቀረባቸው፤ በውኃም አጠባቸው።+ ዘሌዋውያን 8:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 በመቀጠልም የደረት ኪሱን+ አደረገለት፤ በደረት ኪሱም ውስጥ ኡሪሙንና ቱሚሙን+ አስቀመጠ።
30 ኡሪሙንና ቱሚሙን*+ በፍርድ የደረት ኪሱ ውስጥ ታስቀምጣቸዋለህ፤ አሮን በይሖዋ ፊት ለመቅረብ በሚገባበት ጊዜ በልቡ ላይ መሆን አለባቸው፤ አሮን በይሖዋ ፊት በሚቀርብበት ጊዜ ለእስራኤላውያን ፍርድ መስጫውን ዘወትር በልቡ ላይ ይሸከም።