-
ኢያሱ 13:24-28አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
24 በተጨማሪም ሙሴ ለጋድ ነገድ ይኸውም ለጋዳውያን በየቤተሰባቸው ርስት ሰጣቸው፤ 25 ግዛታቸውም ያዜርን፣+ የጊልያድን ከተሞች በሙሉ፣ ከራባ+ ፊት ለፊት እስከምትገኘው እስከ አሮዔር የሚደርሰውን የአሞናውያንን+ ምድር እኩሌታ፣ 26 ከሃሽቦን+ እስከ ራማትምጽጳ እና እስከ በጦኒም እንዲሁም ከማሃናይም+ እስከ ደቢር ወሰን ድረስ ያለውን አካባቢ፣ 27 በሸለቆው ውስጥ* ደግሞ ቤትሃራምን፣ ቤትኒምራን፣+ ሱኮትን፣+ ጻፎንን እና ወሰኑ ዮርዳኖስ ሆኖ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ከሚገኘው ከኪኔሬት ባሕር*+ የታችኛው ጫፍ ጀምሮ ያለውን ቀሪውን የሃሽቦንን ንጉሥ የሲሖንን ንጉሣዊ ግዛት+ ያጠቃልላል። 28 ከተሞቹንና መንደሮቹን ጨምሮ ጋዳውያን በየቤተሰባቸው የያዙት ርስት ይህ ነው።
-