-
ዘኁልቁ 32:1-5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
32 የሮቤል ልጆችና+ የጋድ ልጆች+ እጅግ በጣም ብዙ ከብት ነበራቸው። እነሱም የያዜር+ እና የጊልያድ ምድር ለከብቶች የሚስማማ ስፍራ እንደሆነ አዩ። 2 በመሆኑም የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች መጥተው ሙሴን፣ ካህኑን አልዓዛርንና የማኅበረሰቡን አለቆች እንዲህ አሏቸው፦ 3 “የአጣሮት፣ የዲቦን፣ የያዜር፣ የኒምራ፣ የሃሽቦን፣+ የኤልዓሌ፣ የሰባም፣ የነቦ+ እና የቤኦን+ ምድር 4 ይሖዋ በእስራኤል ማኅበረሰብ ፊት ድል ያደረገው+ ሲሆን ለከብቶች ምቹ ነው፤ አገልጋዮችህ ደግሞ ብዙ ከብት አላቸው።”+ 5 አክለውም እንዲህ አሉ፦ “እንግዲህ በፊትህ ሞገስ ካገኘን ይህ ምድር ለአገልጋዮችህ ርስት ተደርጎ ይሰጥ። ዮርዳኖስን እንድንሻገር አታድርገን።”
-